አማርኛ ጀርመንኛ German 4 Beginners 2.0 Apk
Rate saved, Thank!
4 (1 votes)
Description of አማርኛ ጀርመንኛ German 4 Beginners
Amharisch Deutsch Sprachkurs für Anfänger
ጀርመንኛ - አማርኛ የንግግር መማሪያ
Amharic German for Beginners Speaking Lesson
ጀርመንኛ ለጀማሪዎች
ይህ የአንድሮይድ የሞባይል አፕሊኬሽን የጀርመንኛን ቋንቋ መማር ለሚፈልጉ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተብሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ለጀማሪዎች የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ቃላትንና ለንግግር መነሻ የሆኑ አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችን በአፕልኬሽኑ ያገኛሉ፡፡ አፕሊኬሽኑ የሚጠቀመው ፍላሽካርድ የተሰኘውን የመማሪያ እና የማስተማሪያ ዘዴ ነው ፡፡ ፍላሽካርድ በአንድ ጊዜ አንድን ቃል ብቻ በአንድ ካርድ ላይ በማጥናት በቀላሉ የተማሪ አዕምሮ እንዲያስታውስ የሚያደርግ የመማሪያ እና የማስተማሪያ ዘዴ ነው፡፡ በርግጥ ተማሪው ደጋግሞ ማጥናት ማለትም አፕሊኬሽኑ መጠቀም ይጠበቅበታል፡፡
በየእለት ኑሯችን የምናነሳቸዉ አስፈላጊ ንግግሮች እንዲሁም ጀርመንኛ ተናጋሪዎች የሚያዘወትሩዋቸውን ቃላትም ከነትርጉማቸው በቀላል መንገድ ለማጥናት በሚያመች መልኩ በመደብ በመከፋፈል ተሰናድተዋል፡፡ አፕልኬሽኑ የያዛቸዉ ዋና ዋና ጠቃሚና በንግግር ዉስጥ የምንጠቀምባቸዉ ቃላቶችን ፡- ለምሳሌ ቁጥሮች, ጥያቄዎች, ሰላምታ, ጊዜ, አቅጣጫ, የአየር ሁኔታ, እራስን መግለፅ, ትራንስፖርት, አልባሳት, ሱቅ, ቤተሰብ, የቤት እቃ, ምግብ, ፍራፍሬ, ሰውነት, እንስሳት, ቀለማት, ድርጅቶች, ሆስፒታል, ስራ፣ ሙያ, ሆቴል, … ወዘተ የእነዚህን ዝርዝሮችን ይዟል፡፡
አፕሊኬሽኑ የያዘዉ ነገሮች ከአንድ ጀርመነኛ ቋንቋ ተናጋሪ ጋር ሰላምታ ለመለዋወጥ ለመግባባትና ለመተዋወቅ የምንጠቀምባቸዉ ንግግሮችን፣ ለጉዙ የሚረዱንና የምንጠቀምባቸዉ ቃቶችንና ንግግሮችን፣ በሆቴል ዉስጥ አንድ ነገር አገልግሎት ለማግኘት የምንጠቀምባቸዉን ንግግሮችን፤ በጤና ዙሪያ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ከዶክተር ጋር ለመነጋገር የምንጠቀማቸዉ ንግግሮችን፣ ለመገበያየት እንዲሁም በንግድ አለም ላይ የምንጠቀምባቸዉ ንግግሮችን፤ እና ተያያዥ መረጃዎችን በጀርመንኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በምቹ ሁኔታ ለማንኛዉም የእድሜ ክልል ላለ ሰዉ ታሶቦ የተዘጋጀ የሞባይል አፕሊኬሽን ነዉ፡፡
በተጨማሪም ጀርመን ሀገር በተለያዩ ምክንያቶች ለሚሄዱ ኢትዮጲያዊያን ከጀርመንኛ ተናጋሪዎች ጋር ለመግባባት እንዲረዳቸዉ ታስቦ የተሰራ የሞባይል አፕሊኬሽን ሲሆን ወደ እኛ ሀገር ለሚመጡ ጀርመኖች ጋርም ለመግባባት ይጠቅመናል ፡፡
ይህ Amharic German Speaking Lesson በ OROMNET Software and Application Development PLC, Nekemtie, Ethiopia, የተዘጋጀ ነዉ፡፡
አንዴ ከጫንን ቡኋላ offline በ ኦፍላይን ልንጠቀም እንችላለን፡፡ ለአጠቃቀም ምቹ ስለሆነ ሞባይልዎ ላይ ጭነዉ ይጠቀሙበት፡፡
አፕሊኬሽናችንን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን!
ኦሮምኔት የሶፍትዌር እና የሞባይል አፕልኬሽን ዲቬሎፕመንት PLC ነቀምቴ ኢትዮጵያ
OROMNET Software and Application Development PLC, Nekemtie, Ethiopia